ከ99 በመቶ በላይ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የአንጎል ዕጢን የሚመረምር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞዴል ይፋ ሆነ፡፡

የአንጎል ዕጢ በአስቸጋሪ ቦታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ የህክምና ሂደቱንም ውስብስብ የደርገዋል፡፡

በጀርመን በርሊን በሚገኙ ተመራማሪዎች ይፋ በሆነው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞዴሉ ከ170 በላይ የአንጎል እጢ አይነቶችን እንዲለይ የሚያስችል ስልጠና ወስዷል፡፡

ኔቸር ካንሰር በተባለ መጽሔት ላይ እንደተገለፀው ሞዴሉ ዕጢዎችን በፍጥነት እና በከፍተኛ ትክክለኛነት ይለያል፡፡

ሞዴሉ በርካታ ስልጠናዎችን የሰለጠነ ሲሆን 99.1 በመቶ  የአንጎል ዕጢዎችን  በትክክል ለመመርመር ያስችላል፡፡

ሞዴሉ  በዲ.ኤን.ኤ ናሙናዎች ላይ በመመርኮዝ በትክክል እና  ወጭ ቆጣቢ በሆነ መንገድ የአእምሮ ዕጢን ለመለየትና ለማከም ያስችላል፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም የአንጎል ዕጢን ለመመርመር የሚያስችል ሞዴል ማበልፀጉ ይታወቃል፡፡

ልኡል ወልዴ

ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *