የአዋሽ – ሃራ ገበያ (ወልዲያ) የባቡር መስመር ኘሮጀክት ስራ በነበረዉ ጦርነት ወደ ኋላ እንዲመለስ ሆኗል ተባለ

በዛሬዉ እለት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ40ኛ መደበኛ ስብሰባው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርትን አድምጧል።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸዉን የስራ አፈፃፀም ያቀረቡት ዶ/ር አለሙ ስሜ በ11 ወራት በባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ከ322 ሺህ በላይ ሰዎችንን አጓጉዘናል ብለዋል።

ሚኒስተሩ የግንባታ ኘሮጀክቱ የተቋረጠዉን የአዋሽ – ሀራ ገበያ የባቡር ኘሮጀክት ስራን በተመለከተ ምላሽ ሰጥተዋል።

የአዋሽ – ኮምቦልቻ – ሃራ ገበያ (ወልዲያ) የባቡር መስመር ፕሮጀክትን ግንባታ 90 በመቶ ደርሶ የነበረዉን ስራ በግጭት ምክንያት ወደ ኋላ ተመልሷል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በግጭቱ ምክንያት መቋረጥ ብቻ ሳይሆን የኘሮጀክቱ በርካታ ንብረቶች ተዘርፈዋል ብለዋል።

ሌላዉ የባቡር ኘሮጀክቱን በተመለከተ የኘሮጀክቱ ኮንትራክተር የነበረዉ የቱርኩ ኩባንያ ክስ እንዳቀረበ ተናግረዋል።

ከኩባንያዉ ጋር ያላቀ ጉዳይ እንዳለ ገልፀዉ የኘሮጀክቱን መጠናቀቀቅ እና ቀጣይ ስራ ለመፈፀም ከኩባንያው ጋር የተፈጠረው ችግር ማለቅ እንዳለበት አንስተዋል።

በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠዉ ይህ የባቡር ኘሮጀክት ለሀገሪቱ ልማት ቁልፍ አስተዋጽኦ ከሚያበረከቱ መሰረተ ልማቶች አንዱ እንደሚሆን ተገልፆ ነበር።

ቁምነገር አየለ

ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *