የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተፈጸመው ጥቃት ምን እንዳደረሰ “ባልተለመደ መልኩ አጋንነው”አቅርበውታል ሲሉ ኻሜኒ ተችተዋል።
ይህንን ማድረግ ያስፈለጋቸው ምክንያት ግልጽ ነበር የሚሉት ኻሜኒ “አሜሪካ ያጋነነችበት ምክንያት እውነቱን ለማጣመም እንደሆነ የሰማቸው በሙሉ ይረዳል” ብለዋል።
ኢራን በቀጣናው ከሚገኙ የአሜሪካ ቁልፍ የጦር ሰፈሯቿ በአንዱ ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታውሰው ይህንንም ለማሳነስ ሞክረዋል ሲሉ ገልጸዋል።
አሜሪካ በኢራን የፈጸመችው ጥቃት ኢራንን እጅ የማሰጠት እንጂ በጭራሽ ከኒውክሌር ማበልጸግ ጋር ፍጹም ግንኙነት እንደሌለው የአገሪቱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ኻሜኒ ተናግረዋል።
“አንድ ቀን ስለ ሰብዓዊ መብት፣ ሌላ ጊዜ ስለ ሴቶች መብት፣ ከዚያ ደግሞ ኒውክሌር በመቀጠል ደግሞ ሚሳኤሎች ያነሳሉ” ሲሉ ኻሜኒ ተችተዋል።
ከሳምንት በኋላ የታዩት ጠቅላይ መሪው መሰረታዊው ነገር “ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ነገር ብቻ ነው ፍላጎታቸው፤ ኢራን እጇን እንድትሰጥ” ብለዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
