ሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው፡፡

የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች እየተሰጠ ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የሚኒስቴሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ፈተናውን አስጀምረዋል።

ዘንድሮ በወረቀትና በበየነ መረብ ከ608 ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል ብሏል የትምህርት ሚኒስቴር ።

ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *