በዕዳ ሽግሽጉ ዙሪያ ትናንትና በፈረንሳይ የመጨረሻዉን ስምምነት ገንዘብ ሚኒስቴር ተፈራርሟል ብለዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቀርበዉ ምላሽ እየሰጡ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ በፊት የነበሩት መንግስታት ተበድረዉት የነበረዉን ዕዳ ከሁለት አመት በላይ ስንከራከር ቆይተን 3.5 ቢሊየን ዕዳ መክፈል ችለናል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ 23 ሚሊየን መቀነስ መቻሉንና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ረጅም ርቀት ተጉዘናል ነዉ ያሉት፡፡
ከኢትዮጵያ ዕዳ ላይ 3.5 ቢሊየን ዶላር መቀነስ ብቻ ሳይሆን፤በጥቂት አመታት ዉስጥ ቀይ የነበረዉ የኢትዮጵያ ብድር መጠን ዙሪያ ይህ ምክር ቤት የስራ ዘመኑን ሳይጨርስ ሌላ ዜና እንሰማለን ብለዋል።
ከብሄራዊ ባንክ ምንም ብድር ሳንበደር አመቱን ሙሉ ማሳለፍ ችለናል፤ ይህ ትልቅ ድል ነዉ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ዘንድሮ 9 መቶ ቢሊየን ወጭ መደረጉን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሌላ በኩል 1.2 ትሪሊየን ገቢ መደረጉን በመግለጽ የ3 መቶ ትሪሊየን ልዩነት መኖሩን ተናግረዋል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
