የኢትዮጲያ አመታዊ እድገት ከታቀደው በላይ ሊሆን እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

በኢትዮጲያ በ2017 አ ም ይሳካል ተብሎ ከታቀደው አመታዊ እድገት በላይ ሊሳካ እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአባላቱ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡

የማዕድን ፤ኮንስትራክሽን እና የኢንደስተሪ ዝርፉ ከፍተኛ እመርታ ማምጣቱ በአመቱ ከታቀደው በላይ እድገት ለማስመዝገብ እንደምክንያት ሊቀርብ እንደሚችል ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅሰዋል

ከግብርናው ዘርፍ 3 መቶ ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንዲሁም ከ3 መቶ ሚሊዮን ዶላር 3.5 ቢሊዮን ዶላር ከወርቅ ምርት መገኘቱን አስታውቀዋል

ከሁለቱ ዘርፎች ብቻ በአመቱ ይሳካል ተብሎ ከታቀደው በላይ እጂግ በላቀ መልኩ ማሳከት እንደተቻለ ተናግረዋል

አቤል እስጢፋኖስ

ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *