“በሃኪሞች ጥያቄ ዙሪያ ተስማምተን ተመካከረን ነው የተለያየነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ ምንም ምላሽ አላገኘም ተብሎ የሚወራው ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

የሃኪሞች ጥያቄ ውድቅ የተደረገ ሳይሆን ህጋዊ ጥያቄ ነው ያሉ ሲሆን፤ ነገር ግን በእነሱ ሽፋን ሌላ ጥያቄ መነሳቱን ገልጸዋል፡፡

በተለይም በሃኪሞች ጥያቄ ዙሪያ በነበረን ስብሰባ ተስማምተን ተመካከረን እጅ ተጨባብጠን ነው የተለያየንው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች ገቢ እና ደሞዛቸውን ከሌላ ጎረቤት ሃገር ጋር ማነጻጸር እንደሌለባቸው ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እዚህ ሃገር የምክር ቤት አባልም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ደሞዝ ቅርብ ጎረቤት ሃገር ያለ አንድ ፖሊስ ሊያገኘው እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡

ዋነኛው የእኛ ስራ ግን ሃገራችንን ማገልገል አለብን ብለን ነው እንጂ ለገቢ ከሆነማ ሁሉም መሄድ አለበት ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመንግስት ሰራተኛው፣ መምህሩም፣ ሃኪሙም፣ ወታደሩም ገቢዉ ትንሽ ነው ግን ደግሞ አላማው ሃገሩን ማገልገሉ ነው ብለዋል፡፡

ለዓለም አሰፋ

ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *