ወጣቶች ሥልጣን እንዲለቁ በሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሱባቸው የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በንግድ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ ተቃዋሚዎችን ፖሊሶች “እግራቸውን በጥይት እንዲመቱ” ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንቱ እነዚህ ተቃዋሚዎች እንዳይገደሉ ነገር ግን መሰናከላቸውን አረጋግጡ ብለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በኬንያ ሰኞ፣ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም. በተካሄደው ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ 31 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቀዋል።
ተቋማቱ ፖሊስ ከመጠን ያለፈ ኃይል ተጠቅሟል ሲሉ ከሰዋል።
“የሌላ ሰው የንግድ ተቋምን ወይም ንብረት ሲያቃጥል የተያዘ ማንኛውም ሰው ፖሊስ እግሩን በጥይት መትቶ ሆስፒታል እንዲያስገባው እና ከዚያም ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት።
አትግደሏቸው፤ ነገር ግን መሰናከላቸውን አረጋግጡ” ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ለፀጥታ ኃይሎቻቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ።
ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም
