ተጠርጣሪዎቹ በፑንትላንድ ሰልጥነው ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መሰማራታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ትናንት ባወታው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኑ በመረጃ ክንፍ የተደራጁ እንዲሁም በፋይናንስና በሎጀስቲክ እገዛ ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ፣ ሸገር ከተማ፣ አዳማ፣ ሃሮማያ፣ ሻሸመኔ፣ ባሌ፣ጅማ ፣ ሻኪሶ፣ ከሚሴ፣ በስልጤ ዞን ፣ሃላባ ቁሊቶ ከተማ፤ ጅግጅጋ ከተማና በሐረሪ ክልል በቁጥጥር ውለዋል፡፡
አገልግሎቱ በቁጥጥር ስር ያልዋሉ የሽብር ቡድኑ አባላት ላይ የሚደረገው ክትትል ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አስታውቋል።
ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
