49 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ከራዳር ውጪ መሆኑ ተሰማ

49 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን በሩሲያ ምስራቃዊ ክፍል አሙር ግዛት ከራዳር ውጪ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ደብዛው የጠፋው አውሮፕላኑ አምስት ሕጻናትን ጨምሮ 43 መንገደኞችንና 6 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ እንደነበር የአሙር ግዛት አስተዳዳሪ ቫስሊ ኦርሎቭ ተናግረዋል፡፡

አንቶኖቭ ኤኤን-24 የተሰኘው የመንገደኞች አውሮፕላን ከአሙር ግዛት ብላጎቨሽቼንስክ ወደ ቲይንዳ እያመራ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አሁን ላይ የነፍስ አድን ሰራተኞች ደብዛው የጠፋውን አውሮፕላን የመፈለግ ሒደት መጀመራቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ሀኒፍ ሃምዛ

ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *