ኩባንያው በበጀት አመቱ በቴሌኮም ማጭበርበር እና ስርቆት ተቸግሮ እንደነበር ገለፀ።

በበጀት ዓመቱ 4መቶ62 ሺሕ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎችን ማክሸፉንም ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ተግዳሮቶች ማሳለፉን አስታውቋል።

በማክሮ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ምክንያት የብር የመግዛት አቅም መዳከም እና የውጭ ምንዛሪ እጥረት አንደኛው ችግር እንደነበር ተነግሯል።

ገቢው በአገር ውስጥ ገንዘብ ለሆነ እና ወጪውን በዶላር ለሚያካሂድ ተቋም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የራሱን ችግር ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ግልፅ ነው ሲሉ የተናገሩት የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ናቸው።

አደጋ፣ የጸጥታ ችግሮች፣ የኬብል ስርቆት እና በቴሌኮም መሠረተ ልማት ላይ የደረሱ ጉዳቶች፣ የሀገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮች የአቅም ውስንነት፣ የኃይል አቅርቦት መቆራረጥና የነዳጅ እጥረት ሌሎች ችግሮች እንደነበሩም ገልጸዋል።

ከዲጂታል ዝውውሮች ጋር የተያያዙ የማጭበርበር እንቅስቃሴዎች፣ የባንክ ፈንድ አቅርቦት ላይ ያሉ ገደቦች፣ የደንበኞችን መረጃ ለማረጋገጥ የሚያስችል ሀገራዊ አሰራር አለመተግበር እና የዓለም አቀፍ ትራፊክ መቀነስ ሌላው በበጀት አመቱ አሰራር ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩ ጉዳዮች ነበሩ ብለዋል።

ከፌዴራል እና ክልል የመንግሥት አካላት ጋር በመሥራትና አንዳንድ የቴሌኮም ግብዓቶችን ከአገር ውስጥ አቅራቢዎች በመሸፈን ችግሩን ለመፍታት ጥረት ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል።

ከዛሬ 3 ዓመት በፊት ትግበራ ላይ የዋለው የሊድ/መሪ/ ስትራቴጂ በዚህ በጀት ዓመት 1መቶ62 ቢሊየን ብር ገቢ በማስገባት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።

እስከዳር ግርማ

ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *