የተባበሩት መንግስታት የምግብ ኤጀንሲ፤ናይጄሪያ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ የረሃብ ቀውስ እየተጋፈጠች ነዉ ብሏል፡፡
በናይጄሪያ ወደ 31 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት እየተጋፈጡ መሆኑን እና ህይወትን የሚታደግ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል፡፡
ኤጀንሲው በአፍሪካ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ባለባት ሀገር ቀውሱ የተከሰተው፤ የምግብ ዋጋ መጨመር፣ የዋጋ ግሽበት፣ የምንዛሪ ዋጋ ማሽቆልቆል እና ግጭት እንዲሁም ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳ ጋር ተዳምሮ ነው ተብሏል።
የዓለም ምግብ ድርጅት በአፍሪካ ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እንዲቀንስ ወይም እንዲያቋርጥ የሚያስገድድ ከባድ የገንዘብ እጥረት እየተጋፈጠ መሆኑን አስታዉቋል፡፡
ኤጀንሲዉ በናይጄሪያ የሚደረጉ ስራዎችን ለማስቀጠል በአስቸኳይ 1መቶ30 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገልጾ፤ ቀውሱ በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በምዕራብ እና በመካከለኛው አፍሪካም እየተባባሰ መሆኑን ገልጿል፡፡
ሀኒፍ ሀምዛ
ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም
