ፈረንሳይ በመጪው መስከረም ለፍልስጤም እንደ ሀገር በይፋ እውቅና ልትሰጥ መሆኑን ገለጸች፡፡

ይህም ከታላላቆቹ የG7 ሀገራት መካከል ይህን ያደረገች የመጀመሪያዋ ያደርጋታል።

አሜሪካ እና እስራኤል ይህን ዉሳኔ አዉግዘዉታል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ አገራቸዉ በመጪዉ መስከረም ፍልስጤምን እንደ አገር በይፋ እዉቅና እንደምትሰጣት ገልጸዋል፡፡

የፍልስጤም ባለስልጣናት ውሳኔውን በደስታ የተቀበሉት ሲሆን፤ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው ‹‹ሽብርተኝነትን መሸለም ነው›› ሲሉ ወቅሰዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ዋሽንግተን የፈረንሳዩን ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን የፍልስጤምን መንግስት እውቅና ለመስጠት ያቀዱትን እቅድ ‹‹በጽኑ ትቃወማለች›› ብለዋል፡፡

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለሁለት ሀገር መፍትሄ ለመፈለግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሚያዘጋጀዉ ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቋል።

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲር ኬር ስታርመር፤ የፍልስጤምን አገርነት እውቅና እንዲሰጡ ከፓርላማ አባላት እየጨመረ የመጣውን ጫና ተከትሎ ዛሬ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን መሪዎች ጋር በስልክ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የተባበሩት መንግስታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ በበኩሉ፤ በጋዛ የሰብዓዊ ዕርዳታ ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ እየፈራረሰ ነው ፤ እንዲሁም በረሃብ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ ነዉ ሲል ገልጿል፡፡

አሜሪካ እና እስራኤል በኳታር ሲካሄድ ከነበረው የጋዛ ተኩስ አቁም ድርድር ቡድኖቻቸውን ያስወጡ ሲሆን፤ ዋሽንግተን ሃማስን በቅን ልቦና እየተደራደረ አይደለም በማለት ከሳለች ሲል የዘገበዉ ቢቢሲ ነዉ።

እስከዳር ግርማ

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *