ሶሪያ ከአሳድ መዉደቅ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ምርጫ ልታካሂድ ነዉ፡፡

አገሪቱ ምርጫዉን ከመስከረም 15 እስከ 20 ድረስ እንደምታካሂድ ገልጻለች፡፡

የአሳድ ስርወ መንግስት ወድቆ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አህመድ አል-ሻራ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ የፓርላማ ምርጫ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በታህሳስ ወር ላይ በከፍተኛ ተቃዉሞ ከስልጣናቸዉ ከተነሱት በሽር አል-አሳድ በኋላ የአገሪቱ አዲስ መሪዎች የሚያደርጉት የመጀመሪያዉ ምርጫ ይሆናል፡፡

ካሉት 2መቶ10 መቀመጫዎች ዉስጥ አንድ ሶስተኛዉ የሚሆነዉ በጊዜያዊዉ ፕሬዝዳንት አህመድ አል-ሻራ የሚወከል ሲሆን፤ ቀሪዎቹ መቀመጫዎች ደግሞ ምርጫ ይካሄድባቸዋል ሲል አልጀዚራ ነዉ የዘገበዉ፡፡

እስከዳር ግርማ

ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *