“በጋዛ ውስጥ ረሃብ የለም” ሲል  የእስራኤል የብሄራዊ ደህንነት ሚኒስቴር ገለፀ

የእስራኤል የብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ጊቪር በጋዛ ሰርጥ ውስጥ “ረሃብ “ያለመኖሩን አስታውቋል።

የቀኝ አክራሪው የኦትስማ ይሁዲት ፓርቲ መሪ  በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “ፍልስጤማውያን ቢራቡ  ኖሮ በግዛቱ ውስጥ የታሰሩትን የእስራኤል ምርኮኞች  ይፈቱ ነበር” ብለዋል።

ሃላፊው አክለውም “በጋዛ ውስጥ ፍልስጤማውያን ሳይሆን ሃማስ እንዲራብ ” እደግፋለሁ ነው ያሉት ።

በተባበሩት መንግስታት የሚደገፈው የተቀናጀ የምግብ ዋስትና ደረጃ ምደባ (አይ.ፒ.ሲ) በግንቦት ወር ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ በጋዛ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች አስከፊ ረሃብ ተጋርጦባቸዋል ማለቱ  ይታወሳል።

ቤንጋቪር በዚህ ንግግራቸው ከተለያዩ ሀገራትና አለማቀፍ ተቋማት ውግዘት አስከትሎባቸዋል ተብሏል።

ልኡል ወልዴ

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *