እንግሊዝ የአውሮፓ ሻምፒዮን ሆነች

በሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝ ስፔንን በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆናለች።

የሙሉ ሰአት ውጤት በ 1 አቻ ከ ተጠናቀቀ ቡኃላ ወደ መለያ ምት በማምራት ነው እንግሊዝ የወቅቱ የአለም ሻምፒዮኖቹን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ የቻሉት።

በ2022 የአውሮፓ ሻምፒዮን የነበሩት እንግሊዞች አሁንም ንግስናቸውን ማስጠበቅ ችለዋል።

ሳሪና ዊግማን በሁለት ሀገራት ለሶስተኛ ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫዎችን በማሸነፍ ታሪካዊ አሰልጣኝ መሆን ችላልች።

ስዊዘርላንድ ላይ በተካሄደው በዚህ ውድድር እንግሊዝ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገሯ ውጪ ታላቅ ዋንጫ እንድታሳካ አስችሏታል።

ሀሚድ አብደላ

ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *