የቅዱስ ጳዉሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ከዛሬ ጀምሮ ነጻ የህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡ By ethiofmAdminJuly 28, 2025July 28, 2025የሀገር ውስጥ ዜና ሆስፒታሉ በየዓመቱ እንደሚያደርገዉ በክረምት የበጎ ፍቃድ የጤና አገልግሎት በነጻ ህክምና እንደሚሰጥ አስታዉቋል፡፡ የህክምና አገልግሎቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ከዛሬ ሐምሌ 21 እስከ 27 2017 ዓ.ም ነጻ የህክምና አገልግሎት ለታካሚዎች እንደሚሰጥ መግለጹን ከሆስፒታሉ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡ ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም