በእሁድ ገበያ ላይ ምርቶች እንዲሸጡ ከተተመነላቸዉ ዋጋ በላይ ሲሸጡ በተገኙ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መዉሰዱን የአዲስአበባ ንግድ ቢሮ ለጣቢያችን አስታዉቋል ፡፡
የቢሮው ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ብርሀኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት ከተተመነዉ ዋጋ በላይ ሲሸጡ የተገኙ ነጋዴዎችን በአዲስ ነጋዴዎች የመተካት እርምጃ ተወስዶል ብለዋል ፡፡
የእሁድ ገበያ ለየት የሚያደርገዉ ከሌሎች የገበያ ቦታዎች አንፃር በንፅፅር ሲታይ ከ 15 እስከ 20 ፐርሰንት ቅናሺ መኖሩ ነዉ ብለዋል ፡፡
አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ዉስጥ 5 ግዙፍ የገበያ ማእከላት እና 219 የእሁድ ገበያ መኖራቸዉን አንስተዋል ፡፡
ከከተማ አስተዳደር እስከ ወረዳ ባለዉ ከ1 ሺህ በላይ የቁጥጥር ባለሙያ ተመድቦ የቁጥጥር ስርአት እያተከናወነ መሆኑ ገልፀዋል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም
