በባለፈዉ በጀት አመቱ 230 ዳኞች በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መሠረት ተሹመዉ ነበር።
ይህ የዳኖች ቁጥር በሞት የተለዩ÷ የጡረታ የወጡ እና በዲስፕሊን የተባረሩትን ሳይጨምር መሆኑ ተሰምቷል።
ይህ የተባለዉ የአማራ ክልል ምክርቤት 6ዙር 10 አመት መደበኛ ጉባኤን ባካሄደው መድረክ ላይ ነዉ።
በመድረኩ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የበጀት አመቱን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት አቶ አለም አንተአግደዉ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ ሪፖርቱን እስካቀረበበት ጊዜ ድረስ 181 ዳኖች በአመቱ ስራ ለቅዋል ብለዋል።
127 ወንድ ዳኞች ሲሆኑ 54 የሚሆኑት ሴቶች ዳኞች መሆናቸዉን በሪፖርቱ ተካቷል።
ኘሬዝደንቱ አያይዘውም ከነዚህ መካከል 158 የሚሆኑት በገዛ ፍቃዳቸዉ ስራ የለቀቁ መሆናቸዉን ነዉ ያብራሩት።
ከዚህ ባለፈ በክልሉ ከፍተኛ የዳኞች ፍልሰት እንዳለ የተገለፀ ሲሆን አሁን ላይ 30 የሚሆኑ ዳኞች የስራ መልቀቂያ በማስገባት እየተጠባበቁ እንደሆኑ ሰምተናል።
እንዲህ አይነት ሁኔታዎች የክልሉ ማህበረሰብ እዉቀት እና ልምድ ባላቸዉ ዳኞች የመዳኘት መብትን የሚጎዳ እና ፍትህን የሚያጓድል ነዉ ሲሉ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝደንት ተናግረዋል።
በክልሉ ለምን ዳኖች ስራ እየለቀቁ እንደሆነ የተባለ ነገር የለም
ቁምነገር አየለ
ሐምሌ 23 /2017 ዓ.ም
