በሬክተር ስኬል 8 ነጥብ 8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በሩሲያና ጃፓን ሱናሚ ማስከተሉ ተገለጸ

በአለም ላይ እጅግ ከፍኛ የተባለ በ8 ነጥብ 8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በሩሲያና በሩቅ ምስራቅ አካባቢ ሱናሚ ማስከተሉ የተገለጸ ሲሆን በተለይም በጃፓን እና የአሜሪካዋ ግዛት አላስካ መጠነኛ ማዕበል ተከስቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሃዋይ ሰሜንና መካከለኛው አሜሪካ እንዲሁም የፓስፊክ ደሴቶች እና ደቡባዊ ኒውዝላንድ አቅጣጫ የማዕበል አስጊነቱ በመጨመሩ የማስጠንቀቂያ መልእክቶች ተሰቷል፡፡

በነዚህ አካባዎች የሚገኙ ሰዎች በአፋጣኝ ወደ ከፍታ ቦታዎች ማሳሰቢያ ተላልፉላቸዋል፡፡

ከአላስካ ብሄራዊ ሱናሚ ማስጠንቀቂያ ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት ዴቭ ሲኒደር እንዳሉት በአላስካ አንዳንድ አካባቢዎች የባህር መጠኑ በሰላሳ ሴንቲ ሜትር ከፍ ያለ ሞገድ መታየቱን ገልጸዋል፡፡

በሰሜን ጃፓንም በሃምሳ ሳንቲሜትር ከፍታ የተከሰተ ሱናሚ ማስተዋሉን የጃፓን ሜትሮሎጂ አስታውቋል፡፡፡

ይህ በሰሜን ጃፓን የተከሰተው ሱናሚ ከሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች አንጻር ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡

በአላስካ ካቻትካ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተፈጠረው ሱናሚ በሩሲያ የተወሰኑ ሰዎችን ማፈናቀሉ ተገልጹዋል፡፡

ሆኖም እስካሁን በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተገልጹል ያለው የአሶሺትድ ፕረስ ነው፡፡

ገነነ ብርሃኑ

ሐምሌ 23 /2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *