አገልግሎቱ በአቦል ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ የሚሰጥ ነው።
ባንኩ ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የቀረፀው አገልግሎት መሆኑ ተገልጿል።
አገልግሎቱ ከብሔራዊ የነዳጅ ስርጭት መከታተያ ስርዓት ጋር በመቀናጀት በአገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦት ላይ የሚስተዋል ግልጽነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል የሚያስችል የክፍያ አማራጭ ነው።
ባንኩ የዲጂታል የነዳጅ ክፍያ አገልግሎቱን አዲስአበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች በሚገኙ ማደያዎች ለማስፋፋት ማቀዱ ተገልጿል።
አገልግሎቱ በሙከራ ላይ በዋለበት ጊዜ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ በዲጂታል መዘዋወሩ ነው የተገለጸው።
ደንበኞች የነዳጅ ግዢን መፈፀም የሚችሉት በUSSD፣ አቦል የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን በመጠቀም እንዲሁም በነዳጅ ማደያው የቀረበውን የማጣቀሻ ቁጥር በመጠቀም መሆኑ ተገልጿል።
የዲጂታል የግብይት ስርዓት ወደ ትግበራ ከገባበት 2015 ጀምሮ ግማሽ ትሪሊዮን ብር ተዘዋውሯል ተብሏል።
እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም
