1መቶ 54 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ያሳፈረችዉ ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ ተገልብጣለች ነዉ የተባለዉ፡፡
ቢያንስ 68 የአፍሪካ ፍልሰተኞች በየመን የባህር ዳርቻ ላይ ጀልባ ተገልብጣ መሞታቸውንና ሌሎች 74 ሰዎች ደግሞ መጥፋታቸዉን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ለኤሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪል እንደተናገረዉ፤ 1መቶ54 ኢትዮጵያውያንን ያሳፈረችው ጀልባ በየመን አቢያን ግዛት የባህር ዳርቻ ላይ ተገልብጣለች።
ከመርከቧ አደጋ አስራ ሁለት ሰዎች መትረፋቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የ54 ፍልሰተኞች አስከሬን በባህር ዳርቻ ላይ መገኘቱንና ሌሎች 14 ሰዎች ደግሞ በሌላ ቦታ ህይወታቸው አልፎ ተገኝቶ ወደ ሆስፒታል አስከሬን ማቆያ መወሰዳቸዉ ተነግሯል።
የየመን የጤና ባለስልጣናት ከዚህ ቀደም 54 ሰዎች መሞታቸውን ገልጸው ነበር።
በየመን እና በአፍሪካ ቀንድ መካከል ያለው የውሃ መስመር በሁለቱም አቅጣጫ ለሚጓዙ ፍልሰተኞች የተለመደ ነገርግን አደገኛ መንገድ ነው።
በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ ካለው ግጭት የሚሸሹ አንዳንድ ሰዎች በየመን ጥገኝነት ጠይቀዋል ወይም በአገሪቱ በኩል ወደ ባህረ ሰላጤው አገሮች ለመጓዝ ጥረት አድርገዋል ይላል የ IOM መረጃ።
እንደ IOM ገለጻ፣ መንገዱ በዓለም ላይ ካሉት ‹‹በጣም ስራ ከሚበዛባቸው እና አደገኛ›› ከሆኑ የስደት መንገዶች አንዱ ሆኖ ቀጥሏል።
እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ በ2024 ከ60 ሺህ በላይ ፍልሰተኞች የመን የገቡ ሲሆን፤ ይህም ከቀደመው አመት 97 ሺህ 2መቶ ጋር አጠቃላይ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ የቀነሰ ነው ሲል አልጀዚራ ነዉ የዘገበዉ።
እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም
