በመጥፎ የአየር ጠባይ 157 ሰዎች አሳፍራ የነበረች ጀልባ በመስጠሟ ቢያንስ 68 ስደተኞች ህይወታቸው አልፏል።
መርከቧ ትናንት እሁድ ደቡባዊ የየመን ግዛት በሆነችው አብያን ባህር መስጠሟን የየመን የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ሃላፊ (አይኦኤም) ለቢቢሲ ተናግረዋል። 12 ሰዎች መትረፋቸውን ገልጸው፣ በርካቱች ግን የደረሱበት አልታወቀም።
አብዛኞቹ ተጎጂዎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ይታመናል ሲል አይኦኤም ተናግሯል።
አይኦኤም ክስተቱን “ልብ የሚሰብር” ሲል ገልጾታል።
የመን ከአፍሪካ ቀንድ ወደ ባህረ ሰላጤው ሀገራት ለስራ ፍለጋ ለሚጓዙ ስደተኞች ዋና መንገድ ነች። IOM በቅርብ ወራት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል ወይም ጠፍተዋል ብሎ ይገምታል።
ጀልባዋ ወደ 157 በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳፍራ በአብዛኛው ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የሚጠቀሙበትን አደገኛና ሰፊውን የባህር ዳርቻ መስመርን እየተጠቀመች እንደነበር የአይኦኤም የየመን ኃላፊ አብዱሳቶር ኢሶቭ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የ54ቱ ስደተኞች አስክሬን በደቡባዊቷ የመን ካንፋር ግዛት ዳርቻ የተገኘ ሲሆን የሌሎች 14 ስደተኞች ደግሞ በአብያን ግዛት ዋና ከተማ ዚንጅባር በሚገኝ ሆሰፒታል አስክሬን ማስቀመጫ መወሰዱን አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም
