በሬክተር 5.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ በኢራን ተከሰተ።

ዛሬ ማለዳ ላይ የ5.4 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በደቡብ ምስራቅ ኢራን ተከስቷል፡፡

የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ እንደገለጸው የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር በ08፡36 ሲሆን፤ ጥልቀቱ በግምት 56.7 ኪ.ሜ (35.2 ማይል) ነው።

እስካሁን የመሬት መንቀጥቀጡ ስላደረሰው ጉዳት ከሀገሪቱ ባለስልጣናት የተሰጠ መረጃ የለም።

ኢራን በሴስሚክ እንቅስቃሴ ባለበት ክልል ውስጥ የምትገኝ ሲሆን፤ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ብዙ አውዳሚ የመሬት መንቀጥቀጦችን አስተናግዳለች።

በአገሪቱ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ እጅግ አሳዛኙ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በ2013 ነዉ፡፡

በወቅቱም የ6.7 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ የባም ከተማን በመምታት ቢያንስ የ34 ሺህ ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል ሲል ያስታወሰዉ አናዶሉ ነዉ።

ሀኒፍ ሀምዛ

ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *