አየር መንገድ በዛሬው እለት የ 2017 ዓ/ም አፈፃፀሙን በዛሬው እለት ለሚዲያዎች ይፋ አድርጓል።
አየር መንገዱ በ 2017 ዓ/ም ምን አሳካ፣-
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት።
፣- 6 አለም አቀፍ አዳዲስ መዳረሻዎች በረራ አየር መንገዱ ጀምሯል።(ፓላንድ፣ሻርጃ፣ሞኖሮቢያ እና ሌሎች)
፣-3 Air bus A 350 ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ጨምሮ 13 አዳዲስ አሮፕላኖችን አስገብቷል።
፥-በ 2017 ዓ/ም 15 . 2 ሚሊዮን መንገደኞችን አጓጉዟል።
፥- 3.9 የሀገር ውስጥ መንገደኞች ሲሆኑ ፥ 19 ሚሊዮን አለም አቀፍ መንገደኞች ተጓጉዘዋል።
፥- 7 መቶ 75 ሺ 3 መቶ 23 መቶ ካርጎ ጭነት አጓጉዟል።
፥- አየር መንገድ እጅግ ዘመናዊ የአውሮፕላን ጥገና ወርክሾፕን ጨምሮ ፥ ዘመናዊ መጋዘንን በቅርብ አስመርቋል።
፥-የመንገደኞች ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን አከናውኗል።
፣-አየር መንገዱ የሰው ሀይልን በመደገፍ፣ 1 ሺ 5 መቶ 57 የአቬሽን ባለሙያዎችን አሰልጥኗል።
፥- አየር መንገዱ ለ 5 ሺ ሰራተኞቹ መኖሪያ ቤት እየገነባ ሲሆን ከ አንድ አመት በኃላ ለማጠናቀቅ አቅዷል።
፥-የደንበኞች አገልግሎትን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የተለያዩ ማሻሻያዎችን አድርጓል።
፥- አየር መንገዱ የተለያዩ ሽልማቶችን ማግኘቱን ያስታወሰ ሲሆን በአለም አቀፍ (ስካይ ትራክስ) የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ መሸለሙን አስታውሷል።
አየር መንገዱ ምን ገጠመኝ አለ ?
፥-በመካከለኛው ምስራቅ እና በሌሎችም የአለም ሀገራት ያጋጠሙ ጦርነቶች ለአየር መንገዱ እክል ሆነዋል።
፥- የአለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ።
፥የአሜሪካ መንግስት በየጊዜው የሚያወጣቸው ተለዋዋጭ ህጎች በአቪዬሽን ዘርፍ ላይ ያመጣው ተፅእኖ በአየር መንገዱ ላይ እክል ፈጥሯል።
፥- ወደ አስመራ፣ ጎባ፣ኮንጎ፣ፓርት ሱዳን፣ለመብረር እቅዶች ቢኖሩም በረራውን ማስቀጠል አልተቻለም።
፥-አየር መንገዱ በቀጣይ አመት ሊሰራቸው ካቀዳቸው ፕሮጀክቶች መካከል፥-
፥- አየር መንገዱ 10 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ወጪን በማውጣት በቢሾፍቱ የሚገነባውን ግዙፍ የመንገደኞች መዳረሻ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ።
፥- አየር መንገዱ በቀጣይ ስድስት የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባት።
፥- የኢትዮጲያ አየር መንገድ በቀጣይ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት በተለይ ተመራጭ የአየር መዳራሻ ሆኖ እንደሚቀጥል እና አገልግሎቱን በጥራት እንደሚሰጥ አቶ መስፍን ተናግረዋል።
የውልሰው ገዝሙ
ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም
