ሱዳን የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ከኮሎምቢያ የመጡ ቅጥረኞችን ከአርኤስኤፍ ጎን ለመዋጋት እየላከች ነው ስትል ከሰሰች።

ሱዳን የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሀገሪቱ ወታደሩ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ጋር እያደረገ በሚገኘዉ የእርስ በርስ ጦርነት ፈጥኖ ደራሹን ለመደገፍ የኮሎምቢያ ቅጥረኞችን እየላከች ነው ብላ ከሳለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ፤የሱዳን መንግስት ከኮሎምቢያ እና ከአንዳንድ ጎረቤት የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ቅጥረኞች በኤሚሬት ባለስልጣናት የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ‹‹የማይካድ ማስረጃ›› አለ ብሏል።

መግለጫው ምንም ማስረጃ ያላቀረበ ሲሆን፤ ጎረቤት ሀገራትንም በስም አልጠቀሰም።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ለአሶሼትድ ፕሬስ በላከው ኢ-ሜይል ክሱን ውድቅ አድርጓል።

እስካሁን ግን ከኮሎምቢያ የተሰጠ ምላሽ የለም።

በሱዳን ያለው የእርስ በርስ ጦርነት በሚያዚያ 2023 በካርቱም የተቀሰቀሰ ሲሆን፤ ግጭቱ ከ40 ሺህ በላይ ሰዎችን ለህልፈት ሲዳርግ እስከ 12 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎች ለመፈናቀል እና ብዙዎችን ደግሞ ለርሃብ አደጋ አጋልጧል ሲል የዘገበዉ አፍሪካ ኒዉስ ነዉ።

ሀኒፍ ሀምዛ

ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *