እየተጠናቀቀ ባለዉ 2017 በጀት አመት 1 መቶ 54 አለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በኢትዮጵያ መካሄዳቸዉን የቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል ፡፡
በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ፕሮሞሽንና ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እንደገና አበበ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በአመቱ በተደረጉ አለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ከ 500 እስከ 11 ሺህ ሰዎች የተገኙባቸዉ ነበሩ ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በአመት በአማካኝ ከ17 እስከ 18 የሚደርሱ አለም አቀፍ ኮንፈርንሶች ስታዘጋች እንደነበር የተናገሩ ሲሆን በዚህኛዉ አመት ደግሞ ከ 150 በላይ ኮንፈረንሶችን እንዳዘጋጀች ጠቅሰዋል ፡፡
ነሃሴ መጨረሻ አካባቢ ኢትዮጵያ የአፍሪካ አየር ንብረት ሳምንትን እንደምታዘጋጅ የገለፁት ዶ/ር እንደገና አበበ በቦታዉ ላይ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚጠበቁ አስታዉቀዋል ፡፡
ሃገሪቱ ያላት ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለቱሪዝም ዘርፉ አዳዲስ ገበያዎችን ማምጣቱን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም
