ዋይት ሐውስ ትራምፕ ከሩሲያው እና ከዩክሬኑ መሪ ጋር ለመነጋገር “ዝግጁ” ናቸው አለ

ዶናልድ ትራምፕ መልዕክተኛቸው ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር “በጣም መልካም የሆነ ውይይት” ሲሉ የገለፁትን ውይይት ካደረጉ በኋላ ከሩሲያ እና ከዩክሬን መሪዎች ጋር ለመገናኘት “መልካም ዕድል” እንዳለ ተናገሩ።

በዋይት ሐውስ ሁለቱ መሪዎች ለእንዲህ ዓይነቱ የመሪዎች ጉባዔ ተስማምተው እንደሆን የተጠየቁት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት “በጣም ጥሩ ተስፋ አለ” ሲሉ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ክሬምሊን ቀደም ሲል በፑቲን እና በስቲቭ ዊትኮፍ መካከል ስለተካሄደው ውይይት ግልጽ ያልሆነ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ረዳት ኃላፊው ሁለቱ ወገኖች በሞስኮ “ገንቢ” የሆነው ውይይት ማካሄዳቸውን እና “መልዕክቶችን” መለዋወጣቸውን ተናግረዋል።

የትራምፕ መልዕክተኛ ፕሬዚዳንት ፑቲንን አግኝተው ያናገሩት፣ ሩሲያ በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ የተቀመጠላት ቀነ ገደብ ከማለቁ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ሲሆን ካልሆነ አዲስ ማዕቀብ ይጠብቃታል።

ትራምፕ ረቡዕ ዕለት በኦቫል ኦፊስ አስተያየት የሰጡት በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ ለአንዳንድ የአውሮፓ አጋሮቻቸው ውይይቱን በሚመለከት ማብራሪያ መስጠታቸውን የሚገልጽ ጽሑፍ ከለጠፉ በኋላ ነው።

ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *