በበጀት ዓመቱ 25.18 ቴራ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ተሸጧል ያሉት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ፤ ከዚህም ውስጥ 93 በመቶ ለሀገር ውስጥ እንዲሁም 7 በመቶ ለውጭ ሀገራት ለሽያጭ እንደቀረበ ገልፀዋል።
ከአጠቃላይ ሽያጩ 74.05 ቢሊየን ብር ከኃይል ሽያጭ፤ 1.41 ቢሊየን ብር ከተጓዳኝ አገልግሎቶች መገኘቱንም የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም በማስመልከት ባቀረቡት ሪፖርት ይፋ አድርገዋል።
ኢንጅነር አሸብር ባልቻ በማብራሪያቸው እንዳሉት 60 በመቶ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ 27 በመቶ ለዳታ ማይኒንግ፣ 6 በመቶ ለኢንዱስትሪዎች፣ 5 በመቶ ለኬንያ፣ 2 በመቶው ደግሞ ለጅቡቲ ተሽጧል ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከውኃ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይልን በማመንጨት ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑን ኢንጂነር አሸብር ገልጸዋል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም
