የእስራኤል የጸጥታ ካቢኔ ጋዛ ከተማን ለመቆጣጠር የሚያስችል እቅድ ማፅደቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ኔታንያሁ ቀደም ሲል ሁሉንም የጋዛ ሰርጥ ለመቆጣጠር እንደሚፈልጉ የተናገሩ ሲሆን የፀደቀው እቅድ በተለይ በአከባቢው ትልቁ ከተማ የሆነችው ጋዛ ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡
ከዚህ በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ማስፋፋቷ በፍልስጤም ሲቪሎች እና በእስራኤል ታጋቾች ላይ “አሰቃቂ መዘዝ” ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል።
የጋዛ ከተማን መቆጣጠር ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የመጀመሪያው ምዕራፍ ሊሆን እንደሚችል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት በካቢኔው በአብላጫ ድምጽ የጸደቁ የጋዛ ከተማን ለመውረር እንዲሁም ጦርነቱን የመቋጨት አምስት መርሆዎችን እቅዶችን ዘርዘር ያለ መግለጫ አውጥቷል።
“የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የጋዛን ከተማ ለመቆጣጠርና ከጦርነቱ ቀጣና ውጭ ላሉ ሰላማዊ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታም ለመስጠት ይዘጋጃል” ብሏል።
የእስራኤል መከላከያ ጦርነቱን ለመቋጫት መርሆዎች ያላቸውንም ዘርዝሯል።
አምስቱ ተብለው የተዘረዘሩት ሐማስን ትጥቅ ማስፈታት፣ ሁሉንም ታጋቾች መመለስ (በህይወት ያሉ እንዲሁም የሞቱትን አስከሬኖቻቸውን)፣ የጋዛን ሰርጥ ከወታደራዊ ትጥቅ ነጻ ማድረግ፣ ጋዛን የሚያስተዳድረውን ሐማስን በማስወገድ እንዲሁም ዌስት ባንክን ከሚያስተዳድረው የፍልስጤም አስተዳደር ውጭ የሆነ አማራጭ የሲቪል መንግሥት ምስረታን ያካተተ ነው።
ሐመረ ፍሬው
ነሐሴ 2/2017 ዓ.ም
