የሲዳማ ቡና ይግባኝ ክስ መቋረጡ ተገለጸ !

ሲዳማ ቡና ለአለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ክስ ሂደት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የፋይናንስ መመሪያን ተላልፈው የተገኙ ክለቦች እና ተጨዋቾች ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ ማፅናቱ ይታወሳል።

ክለቦቹ በበኩላቸው ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድቤት በመውሰድ የተጫዋቾቹን እግድ አስነስተናል በሚል ተጨዋቾቹን መጠቀም ቀጥለው ነበር።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ የኢትዮጵያ ዋንጫን ጨምሮ ክለቦቹ ያልተገቡ ተጫዋቾችን ያሰለፉባቸው ጨዋታዎች በሙሉ በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆኑ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጉዳዩን ወደ ዓለምአቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድቤት (CAS) በመውሰድ ይግባኝ ጠይቋል።

በቅርቡ ሲዳማ ቡና የክስ ሂደቱ በሚታይበት ወቅት የፌዴሬሽኑ ውሳኔ በጊዜያዊነት እንዲታገድ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆኖም ነበር።

ካስ በዛሬው ዕለት ሲዳማ ቡና ያስመዘገበው የይግባኝ ክስ በፍርድቤቱ መመሪያ (CAS Code) መሰረት የቅደም-ተከተል ሂደቱን ያልተከተለ እና የይግባኝ ፍሬ ሃሳቡ በሰነድ መልክ ያልቀረበበት በመሆኑ

  • የተቀመጠው ቀነ ገደብ ካለፈ በኋላ ክለቡ በማስተካከያነት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ
  • የይግባኝ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ በመወሰን
  • የኬዝ ፋይሉን መዝጋቱን በፍርድቤቱ የይግባኝ ግልግል ክፍል ምክትል ፕሬዘዳንት ፊርማ በወጣ የትዕዛዝ ደብዳቤ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽ በበኩሉ የፍርድ ሂደት ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ ለመገናኛ ብዙሃን እንደሚያብራራ ገልጿል ያለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽ ነው፡፡

ነሐሴ 2/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *