ምክክሩ ከቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ ጋር ምንም የሚጋጭ ነገር የለውም ሲል የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።

የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳውን ሰብስቦ ምክክር ለማድርግ ከቀጣዪ ሃገራዊ ምርጫ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለውም ሲል ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

የሃገራዊ ምክከር ኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ምርጫው በምርጫ ቦርድ ሰዓት እና ጊዜ የሚካሄድ ነዉ፤ ይህ ደግሞ ከምክክሩ ጋር ምንም የሚጋጭ ነገር የለውም ብለዋል፡፡

በቀጣዩ አመት ኮሚሽኑ እና ቦርዱ ሁነቶቻቸዉን ለማካሄድ ማቀዳቸውን ተከትሎ መደራረብ አይፈጠርም ወይ የ
ሚል ጥያቄ በመነሳቱ ነው ይህን ምላሽ የሰጡት።

ቃል አቀባዩ ላለመጋጨቱ እንደምክንያት ያነሱት “የምክከር ኮሚሽኑ ተራዝሞ የተሰጠው ቀነ ገደብ ከ ምርጫው ቀደም ብሎ በመጠናቀቁ ነው።

ኮምሽኑ የተሰጠው የስልጣን ጊዜ ሊያበቃ የስድስት ወራት የእድሜ ገደብ ይቀረዋል።

ከምርጫ ጋር በተያያዘ ደግሞ እየተጣጣሙ የሚሄዱ ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ አመት የስራ ዘመኑ ተራዝሞ አሁን ላይ ወደ ስድስት ወር ገደማ እንደቀረዉ ያነሳዉ ኮሚሽኑ፤ በተቀሩት ጊዜያት የቀሩ አጀንዳዎችን በማሰባሠብ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ተገልጿል።

ለዓለም አሰፋ

ነሐሴ 6 /2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *