አሜሪካ እና ቻይና የታሪፍ ጭማሪው ተግባራዊ መሆን ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት የንግድ ሥምምነታቸውን እስከ ሕዳር10 ድረስ አራዘሙ።
የዓለማችን ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆኑት ሁለቱ አገራት በጋራ ባወጡት መግለጫ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ እያንዳንዳቸው በሚያስገቧቸው ምርቶች ላይ የሦስት አሃዝ ታሪፍ ለመጣል ያስተላለፉትን ውሳኔ ለተጨማሪ 90 ቀናት ማራዘማቸውን ገልፀዋል።
ሁለቱ አገራት ባለፈው ወር ያጠናቀቁትን ውይይት “ገንቢ” በማለት ጠርተውታል።
የቻይናው ከፍተኛ ተደራዳሪ በወቅቱ እንደተናገሩት ሁለቱ አገራት ስምምነቱን ለማስቀጠል እንደሚጥሩ የገለፁ ሲሆን፤ የአሜሪካ ባለስልጣናት በበኩላቸው ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመጨረሻውን ይሁንታ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረው ነበር።
ሰኞ ዕለት ዶናልድ ትራምፕ የታሪፍ ስምምነቱን ለማራዘም ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ ፈርመዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም
