ከ 65 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን በተሀድሶ ስልጠና ሂደት ማሳለፉን ኮሚሽኑ ገለጸ።

ኮሚሽኑ የፕሮግራሙን ትግበር ከጀመረበት ከህዳር 2017 ጀምሮ እስካሁን ድረስ በትግራይ፣ አፋር፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ የታጠቁ ኃይሎችን ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን አስታዉቋል፡፡

በትግራይ ክልል ከ53 ሺህ በላይ፣ በአፋር ከ1ሺህ7መቶ በላይ፣ በአማራ ከ5 ሺህ በላይ እና በኦሮሚያ ከ5 ሺህ 3መቶ በላይ መመለሳቸዉ ተገልጿል።

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ተዋጊዎችን በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ሂደት በማሳለፍ የማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ድጋፍና የሲቪክ ስልጠና መስጠቱን አስታዉቋል፡፡

የዲጅታል መታወቂያ በመስጠት ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጋቸዉም ተገልጿል።

ከፌደራል መንግስት እንዲሁም ከክልሎች ከ1.7 ሚሊየን ብር በላይ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ደግሞ ከ5.9 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉም ተነስቷል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *