የህዝብን ገንዘብ አላግባብ መጠቀም ጋር በተያያዘ ምርመራ ሲደረግባቸዉ ቆይቷል፡፡
ከምርመራዉ በኋላም በሙስና ወንጀል ተይዘው መታሰራቸዉ ተሰምቷል፡፡
የሀገሪቱ ኦዲተር ጄኔራል ጽህፈት ቤት በማይጋ አመራር ስር የመንግስት ገንዘብ ተዘርፏል የሚል ጥርጣሬን በመጥቀስ ነበር ሰነዶችን ለፍርድ ቤት ያስረከበዉ፡፡
ምርመራው የተከፈተው በማይጋ የስልጣን ዘመን ከህዝባዊ ፕሮጀክት ምረቃ ጋር በተያያዙ አጠራጣሪ ወጪዎች ላይ እንዲሁም ምክንያታዊነት የጎደላቸው የሚባሉ ተልዕኮ ነክ ክፍያዎች ላይ ተመስርቶ ነው።
ማሊ ከ2020 ጀምሮ በወታደራዊ መሪዎች እየተመራች ሲሆን፤ ወታደራዊዉ መንግስት ስልጣኑን በኃይል ከያዘ በኋላ በሚቀጥለው አመት ሌላ መፈንቅለ መንግስት አካሂዷል።
የሀገሪቱ መሪ ጄኔራል አሲሚ ጎይታ፤ ወታደራዊዉን መንግስት በ2024 ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመመለስ ቃል ቢገቡም ተጨማሪ አምስት አመታትን በስልጣን ላይ ቆይተዋል፡፡
ማይጋ በ2021 ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በህዳር 2024 ከስልጣናቸው ተነስተዋል።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ደጋፊዎች አሁንም ተቃውሞ ላይ ሲሆኑ፤ ድርጊቱንም የፖለቲካ አላማ አለው ሲሉ መግለጻቸዉን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።
ሀኒፍ ሀምዛ
ነሐሴ 7/2017 ዓ.ም
