የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመታዊ የቴሌቪዥን ግብርን መቀበል ሊያቆም እንደሚችል ፍንጭ ሰጠ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1278/2015 ዓ.ም በተሰጠው ስልጣን መሰረት አመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ቢል ጋር እንዲሰበስብ መወሰኑ የሚታወቅ ነዉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዚህ መንገድ የቴሌቪዥን ግብር እየሰበሰበ እንዳለ ቢታወቅም አመታዊ የቴሌቪዥን ግብር ቤት ለቤት እየተጠየቀ እንደሆነ ከማህበረሰቡ ተሰምቷል ።

አመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ግብርን ቤት ለቤት እየተጠየቅን ነዉ በሚል ከደንበኞች ቅሬታ መነሳቱ የሚታወስ ነዉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ላይ አገልግሎት ይህን የቴሌቪዥን ግብር መሠብሰብ አቋርጧል ወይ ? የሚል ጥያቄ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ ጥያቄዉን ሲመልሱም “ጉዳዩን እንደሰማን ከኢትዩጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ለመነጋገር ሞክረናል” ብለዋል።

ደንበኞች ይህንን ግብር ሁለት ጊዜ መክፈል እንደሌለባቸዉ በመነጋገር ይህንን እንደሚያርሙ ነግረዉናል ሲሉ ስራ አስፈፃሚዉ ተናግረዋል።

ሆኖም ተቋሙ ይህንን ማረም እና ማስተካከል ካልቻለ ግን ደንበኞችን ማስቀየም ስለማያስፈልግ ዉሉን ወደ ማቋረጥ እንደሚሄዱ አገልግሎቱ ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ አስታዉቀዋል።

ቁምገር አየለ

ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *