ሐማስ በቀረበለት የጋዛ የተኩስ አቁም ላይ መስማማቱ ተሰምቷል

ሐማስ ከእስራኤል ጋር በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾችን ለመልቀቅ በአሸማጋዮቹ የቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ መስማማቱን ምንጮች ለቢቢሲ ገለፁ።

ግብፅ እና ኳታር ያቀረቡት ምክረ ሃሳብ የአሜሪካ ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ በሰኔ ወር ባቀረቡት ማዕቀፍ ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል።

በመጀመርያው 60 የተኩስ አቁም ቀናት ሐማስ ከቀሩት 50 እስራኤላውያን ታጋቾች መካከል ግማሹን፣ 20ዎቹ በሕይወት እንዳሉ ይታመናል፣ በሁለት ቡድን በመክፈል የሚለቅ ይሆናል።

በዚሁ ወቅት ቋሚ የተኩስ አቁም ላይ ድርድር ይኖራል ተብሏል።

የጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት ባለፈው ሳምንት ስምምነቱን ሊቀበል የሚችለው “ታጋቾቹ በሙሉ በአንድ ጊዜ የሚለቀቁ ከሆነ ብቻ ነው” ማለቱን ተከትሎ ምላሹ ምን ሊሆን እንደሚችል ግልፅ አይደለም።

ነሐሴ 13 /2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *