ሐሙስ ዕለት በቺሊ በስተደቡብ በድሬክ መተላለፊያ 7.5 ማግኒቲዩድ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂ ጥናት ተቋም (USGS) አስታውቋል።
በቺሊ እና በአጎራባች አርጀንቲና በሚገኙ በርካታ ከተሞች የመሬት መንቀጥቀጡ ተሰምቷል።
እስካሁን የተገለፀ ምንም ዓይነት የጉዳት ሪፖርት የለም።
ከመንቀጥቀጡ በኋላ የቺሊ የባህር ሃይድሮግራፊክ እና ውቅያኖስ ጥናት አገልግሎት (SHOA) የሱናሚ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ሲሆን የባህር ዳርቻ አካባቢዎችን ለቅቆ ለመውጣት ትዕዛዝ አስተላልፏል።
መንቀጥቀጡ በመጀመሪያ አደገኛ የሱናሚ ሞገዶች እንዲፈጠሩ ያደረገ ቢሆንም፣ የፓሲፊክ ሱናሚ ማስጠንቀቂያ ማዕከል በበኩሉ ለብሉምበርግ በላከው ኢሜል ላይ ስጋቱ መወገዱን አረጋግጧል።
በዚህም ምክንያት የሚፈጠሩ የባህር ዳርቻ ሞገዶች ከ 0.3 ሜትር (1 ጫማ) በላይ ከፍታ እንደማይኖራቸው ተቋሙ ጨምሮ ገልጿል ሲል የዘገበው አናዶሉ ኒውስ ነው።
ሀኒፍ ሀምዛ
ነሐሴ 16 /2017 ዓ.ም
