በአማራ ክልል 2መቶ74 እናቶች ከወሊድ ጋር በተያየዘ ህይወታቸዉ ማለፉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታዉቋል፡፡
ለእናቶች ሞት መንስኤ ምንድነዉ የሚለዉን በጥናት ለማረጋገጥ ተሞክሯል ሲሉ የክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች ወጣቶች እና ህፃናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልሰዉ ጫንያለዉ ለጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በዚህም ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት እናቶች በወሊድ ጊዜ በሚያጋጥም የደም መፍሰስ እንደሚሞቱ መታወቁን ገልፀዋል፡፡
በተለይ በክልሉ የፀጥታ ችግር ባለባቸዉ አካባቢዎች የጤና ተቋማት መዘጋት ለችግሩ ሌላኛዉ ተጠቃሽ ጉዳይ ነዉ ብለዋል፡፡
አምቡላንሶች በተፈለገዉ ልክ ተንቀሳቅሰዉ እንዳይሰሩ እክል እንደተፈጠረም አቶ መልሰዉ አንስተዋል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ነሐሴ 16 /2017 ዓ.ም
