በመዲናዋ ሶስት የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቻ አዲሱን የዳግም ምዝገባ መስፈርት ያሟሉት ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አሰራር ስርዓት ለማስያዝ በሚል ዳግም ምዝገባ በማካሔድ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ የወጣዉ መመሪያ 988/2016 ሆኖ መፅደጉን ተከትሎ የስራ አፈፃፀሙን ባለስልጣኑ ይፋ አድርጓል።

በዚህም በተገኘዉ ዉጤት በተደረጉ ሶስት ተከታታይ ዙር የመመዘኛ ጊዜያት በከፊል በሁኔታ መስፈርት መስፈርቱን ያሟሉት 3 ተቋማት ብቻ መሆናቸዉን ገልፆል።

ከዚህም ዉስጥ ሁለት ዩንቨርስቲዎች እንዲሁም 1 ኮሌጅ መሆኑን ነዉ ባለስልጣኑ የገለፀዉ ፡፡

በግምገማ ወቅት ለመስክ ምልከታ አብዛኞቹ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቂ አለመሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ ሲል ባለስልጣኑ ገልፀዋል።

በመሆኑም በሁኔታ የሚል የመገምገሚያ መስፈርት የሚገመገሙበት አግባብ ተፈጥሯል ተብሏል።

ግምገማዉ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ በሚገኙ የግል ከፍተኛ ተቋማት የሚገኙት ላይ ብቻ መካሄዱ ተነግሯል።

በዚህም ከሶስት ተቋማት÷ በሶስት ካምፓሶች እንዲሁም አስራ ስምንት የትምህርት ክፍሎች በከፊል መስፈርቱን ያሟሉ ሆነዉ መገኘታቸዉን ነዉ ባለስልጣኑ የገለፀዉ።

ባለስልጣኑ የዳግም መዝገባ መመሪያ ዉስጥ ያካተተዉ መመዘኛ ተቋማቱ ስጋት ላይ የሚጥሉ እንደሆኑ ተቋማቱ እየገለፁ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም ባለስልጣኑ የዳግም ምዝገባ ማድረግ ያልቻሉ 85 ተቋማት ከዘርፋ መውጣታቸውን ተነግሯል።

አሁንም እየተደረገ ባለዉ የዳግም ምዝገባ ሥራዎች መስፈርቱን ያላሟሉ ተቋማት የጊዜ ገደብ እንደተቀመጠላቸዉ ነዉ ባለስልጣኑ የተናገረዉ።

ሆኖም ተቋማቱ የተቀመጡ መስፈርቶች የትምህርት ጥራት ለሟሟላት ግንኙነት የሌላቸዉ እና አቅም የሚጠይቁ መሆናቸዉን ገልፀዉ አሁንም መስፈርቶቹ እንዲታይ እየጠየቁ ይገኛል።

ቁምነገር አየለ

ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *