የእስራኤል ጦር አዛዥ በጋዛ የእስረኞች ልውውጥን በተመለከተ የቀረበውን ሀሳብ እንዲቀበሉ ኔታንያሁን ጠይቀዋል፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ኢያል ዛሚር፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቀረበው የእስረኞች ልውውጥ ሀሳብ ላይ ስምምነት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የጋዛ ከተማን መቆጣጠር በእስራኤላውያን ታጋቾች ህይወት ላይ “ከባድ አደጋ” ሊያስከትል እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል።

ሐሙስ ዕለት ኔታንያሁ የጋዛ ከተማን የመቆጣጠር እና የነዋሪዎቿን የማስፈር እቅድ ማስፈጸም በሚቀጥሉበት ወቅት ሁሉም ታጋቾች እንዲፈቱ በአፋጣኝ ድርድር እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ አሸማጋዮች ከግብፅ እና ኳታር በቀረበው ሀሳብ ላይ ከእርሳቸው ይፋዊ ምላሽ እየጠበቁ ሲሆን፤ ይህ ሀሳብ ከቀደምት የእስራኤል ስምምነቶች ጋር የሚጣጣም እና በቅርቡም በሃማስ ተቀባይነት አግኝቷል።

ጦሩ ለስምምነቱ መጠናቀቅ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፤ውሳኔው አሁን በኔታንያሁ እጅ ላይ ነው ብለዋል።

የጦሩ አዛዥ የጋዛ ከተማን ለመቆጣጠር በታቀደው እቅድ ላይ ያላቸውን ስጋት በድጋሚ ገልጸዋል።

ጦሩ ጋዛን የመቆጣጠር አቅም አለው፤ ነገር ግን ይህ ዘመቻ የታጋቾችን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል ብለዋል።

እስራኤል፣ ሃማስ በህይወት ያሉ 20 ሰዎችን ጨምሮ 50 ታጋቾችን እንደያዘ ገምታለች።

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች በእስር ላይ የሚገኙ ፍልስጤማውያን ላይ ስቃይ እና የህክምና ቸልተኝነት እየደረሰ መሆኑን ሪፖርት በሚያደርጉበት ወቅት፤ቴል አቪቭ ከ10 ሺህ 8መቶ በላይ ፍልስጤማውያንን አስራለች ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ።

እስከዳር ግርማ

ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *