አሜሪካ በስህተት ወደ ኤል ሳልቫዶር አባራው የነበረውን ግለሰብ በድጋሚ ለማባረር ያቀረበችው ሃሳብ በጊዜያዊነት ታገደ

አሜሪካ በስህተት ወደ ኤል ሳልቫዶር አባራው የነበረውና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደገና የመለሰችውን ግለሰብ በድጋሚ ወደ ሶስተኛ አገር ለማባረር ያቀረበችው ሃሳብ በፌደራሉ ዳኛ በጊዜያዊነት ታገደ።

የፌደራሉ ዳኛ ኪልማር አብሬጎ ጋርሺያ የተባለው ግለሰብ ወደ ሶስተኛ አገር ምናልባትም ወደ ኡጋንዳ መባረሩን በጊዜያዊነት አግደዋል።

ይህንንም እገዳ ተከትሎ በአውሮፕላን ሊሳፈር የነበረው ኪልማር በኢሚግሬሽን ባለስልጣናት አማካኝነት በእስር ወደሚቆይበት ስፍራ ተወስዷል።

የአሜሪካ መንግሥት ጋርሺያን በስህተት ኤል ሳልቫዶር ወደሚገኝ ነውጠኛ እስር ቤት አስገብቶት የነበረ ሲሆን በመጨረሻም መጋቢት ወር ላይ ወደ አሜሪካ መልሶ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ መስርቶበታል።

ጋርሺያ የቀረበለትን የጥፋተኝነት ውል ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኑ የአሜሪካ ባለስልጣናት ወደ ኡጋንዳ እንደሚያባርሩት መንገራቸውን ጠበቆቹ ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *