ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 2መቶ35 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ገለፀ።

የደንበኞቼን ቁጥርም 88 ሚሊየን ለማድረስ አቅጃለሁ ብሏል።አሁን የደንበኞቹ ቁጥርም 83.2 ሚሊየን።

ኩባንያው ሊድ ብሎ የሰየመው የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ሲጠናቀቅ ያገኘው ገቢ 1መቶ62 ቢሊየን ብር ነበር።

ዛሬ ይፋ ባደረገው አዲስ የሶስት ዓመት “ቀጣዩ አድማስ” በተሰኘው ስትራቴጂ፤ በ2018 73.8 ቢሊየን ብር ጭማሪ በማድረግ 2መቶ35.8 ቢሊየን ብር ለማስገባት አስቧል።

የደንበኞቹን ቁጥርም በ6 በመቶ በማሳደግ 88 ሚሊየን አደርሳለሁ ብሏል።

የቴሌብር ደንበኞች ቁጥርም ከ54.8 ሚሊየን ወደ 62.5 ሚሊየን ለማሳደግ መታቀዱም ተገልጿል።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ በበጀት ዓመቱ የተለያዩ ችግሮች ሊያጋጥሙን እንደሚችሉ ብናውቅም መፍትሄዎችም አዘጋጅተናል ብለዋል።

ይህ የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ሲጠናቀቅ 1 ትሪሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅደን ነበር ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፤ የተለያዩ ስሌቶችን ከሰራን በኋላ 8መቶ42 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅደናል ብለዋል።

በውጭ ምንዛሪም 9መቶ76 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ገልፀዋል።

በዚህ ሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥም የቴሌብር ደንበኞቹን ቁጥር 75 ሚሊየን ለማድረስ አስቧል።

በቴሌብር የሚደረግ የገንዘብ ዝውውር መጠን 21.3 ትሪሊየን ለማድረስ በዕቅድ መያዙንም ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ሊድ የተሰኘ የ3 አመት የዕድገት ስትራቴጂ በመስከረም ወር 2015 ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፤ የዛሬ ወር ገደማ መጠናቀቁ ይታወሳል።

እስከዳር ግርማ

ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *