በፈናን ፔይ ሶሉሽንስ አክሲዮን ማህበር የበለፀገውና በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው ፈናን ፔይ የዲጅታል ክፍያ ስርዓት በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል
ፈናን ፔይ የዲጅታል ክፍያ ስርዓት በአገልግሎት ሰጪዎችና በደንበኞቻቸው መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ የመስመር (online/electronic payment) ላይ ግብይቶችን ለማመቻቸት የተነደፈ የክፍያ ዘዴ ነዉ ፡፡
ፈናን ፔይ በባንክ ሥራ ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተመሠረተ ከመሆኑ አንፃር ቴክኖሎጂው አስተማማኝ መሆኑን በተግባር ጭምር መረጋገጡ ተገልጿል።
በፈናን ፔይ ሶሉሽንስ አክሲዩን ማህበር የበለፀገዉ ፈናን ፔይ የዲጅታል የክፍያ ስርዓት ድርጅቶች የኦንላይን መተግበሪያቸው ሁሉንም የክፍያ አማራጮች እንዲኖራቸው የሚረዳ ነዉ ተብሏል ፡፡
በኢንተርኔት የሚደረጉ ክፍያዎችን የሚያሳልጥ፣ የንግዱ ማኀበረሰብ ግብይትን ከባንኮች ጋር የሚያስተሳሰር የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን እንደሚተገብር ተገልጷል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም
