ቅርጫን ጨምሮ ለግል ፍጆታ የሚደረግ እርድ ቢቻል በቄራዎች እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ቅርጫን የሚከለክል አቋም ባይኖርም ሆኖም ህብረተሰቡ ለሚያደርገው እርድ አስፈላጊውን የእርድ ተግባራት ማከናዉን ያስፈልገዋል ተብሏል።

በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት÷ የልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር እንዲሁም የአርሶ አደር እና የከተማ ግብርና ልማት ኮምሽን በጋራ በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

መጪዉ በአል ጨምሮ በመስከረም ወር ከ42 ሺህ በላይ እርድ ለመፈፀም እቅድ መያዙ ተነግሯል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደር እና የከተማ ግብርና ልማት ም/ኮምሽነር ዶ/ር ፀጋ ለማ በሶስቱም ቄራዎች ላይ አስፈላጊዉ ቅድመ እና በድህረ እርድ ዙሪያ ያሉ ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን አንስተዋል።

ለቤተሰብ ፍጆታ እንዲዉል የሚፈፀሙ እርዶች እንዲሁም የቅርጫ እርድ ቢቻል እያንዳንዱ ቄራዎች ላይ መደረግ አለበት የሚል ማሳሰቢያ እንዳለ የገለፁት ዶ/ር ፀጋ በቀጣይ ያን ለማድረግ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

መግለጫዉን የሰጡት ተቋማት በተለይም ማህበረሰቡ ከህገወጥ እርድ መጠንቀቅ እና መገንዘብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት በተደረገ የክትትል እና የቁጥጥር ስራ 350 ያህል የተጠጉ ልኳንዳ ቤቶች ከህገወጥ የስጋ ዝዉዉር ጋር በተያያዘ እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ ዶ/ር ፀጋ ተናግረዋል።

የስጋን በማጓጓዝ ላይ ስራ የሚፈጠር ብክለት ለመቀነስ በአመቱ ደረጃ በማዉጣት ስጋ የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች በመመዘን ወደ ስራ ተገብቷል ተብሏል።

በባለፈው አመት 40 ተሽከርካሪዎች የታገዱ መሆኑን ዶ/ር ፀጋ አስታዉሰዉ አሁን ላይ በማህበር ተደራጅተዉ የመጡት ደረጃቸዉን መጠበቃቸዉ ተረጋግጦ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የከተማ ግብርና ኮሚሽን እንዲሁም ከመዲናይቱ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ትኩረት በመስጠት ህገወጥ እርድን ለመከላከል ክትትል እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።

ቁምነገር አየለ

ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *