በጥቁር ዘር ታሪክ “የመጀመሪያው ታላቅ ሥራ ሕዳሴ[ግድብ] ነው” አሉ ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በዛሬው እለት በታላቅ ድምቀት በተመረቀው የሕዳሴ ግድብ ላይ ባደረጎት ንግግር “ ሕዳሴ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝቦች በሙሉ ምድር አስክትሰበሰብ ታሪክ ሆኖ የሚኖር ታላቅ ገድል ነው“ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሕዳሴ የትላንት ቁጭት ማሰሪያ፣ የመጪው ንጋት ማብሰሪያ መሆኑን በመግለጽ ሰባ አራት ትሪሊየን ሊትር ውሃ የያዘው ንጋት ሐይቅ ብቻ፣ አሁን ላይ 15 ቢሊዮን ብር ከሆነው የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) የላቀ ሀብት ይዞ በመምጣቱን ተናግረዋል፡፡

“ከእዚች እለት ጀምሮ፣ ዳግም አድዋ በጉባ ላይ በዚህ ትውልድ በመሠራቱ የኢትዮጵያ የልመና፣ የኢትዮጵያ የስንፍና፣ የኢትዮጵያ የእንጉጉሮ ዘመን አብቅቶ እንደ ልኳ የምትለካበት ዘመን ከፊታችን ተዘርግቶ፣ ልክ ትናንትና እሁድ እንደነበረው፣ ዛሬ ሰኞ እንደሆነ፣ ቅድም ጠዋት እንደሆነ፣ አሁን ረፋድ እንደሆነው እንደዚሁ በግልጽ የሚታየው ነገር የኢትዮጵያ ብልጽግና እና የኢትዮጵያ ልክ አይቀሬ መሆኑ ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች፣ ኢትዮጵያ ረጂነቷ አምጥቶ ረጂ ትሆናለች።”

ኢትዮጵያ ግድቡን የተገነባው የጥቁር ሕዝብ ታሪክ ለመቀየር እንጂ በፍጹም ወንድሞቿን ለመጉዳት አለመሆኑን እና ሀገራቸው በድጋሚ እንደሚያረጋግጡላቸው አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

“የግብጽ ረሀብ፣ የሱዳን ረሀብ የሌሎች ወንድሞቻችን ረሀብና ችግር የእኛም ረሀብ ስለሆነ አብረን ከመብላት፣ ከመካፈል ውጪ እኛ ተጠቅመን ማንንም የመጉዳት መሻት፣ ፍላጎት ስለሌለን፤ ያለፈው አልፏል ለወደፊት በምንሰራቸው ታላቅ ስራዎች በትብብር በጋራ እንድንቆም ከወዲሁ ከአደራ ጭምር ላሳስባችሁ እወዳለሁ።” ብለዋል፡፡

ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *