ፖላንድ የአየር ክልሌን ጥሰዋል ያለቻቸውን የሩሲያ ድሮኖች መትታ ጣለች

አውሮፓዊቷ አገር ፖላንድ፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት በምትፈፅምበት ጊዜ የአየር ክልሌን ጥሷል ያለችውን ሰው አልባ አውሮፕላን ( ድሮን) መሳይ አካላት መትታ መጣሏን ገለጸች።

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ( ኔቶ) አባል የሆነችው ፖላንድ፣ ከሦስት ዓመታት በፊት የዩክሬን ጦርነት ከጀመረ ወዲህ በአየር ክልሏ ውስጥ የሩሲያ ንብረት የሆነን አካል መትታ መጣሏን ስትገልጽ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ተስክ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ስለተፈጠረው ሁኔታ እና አገራቸው የአየር ክልሏን ጥሰው በገቡ አካላት ላይ ስለወሰደችው እርምጃ ለኔቶ ዋና ኃላፊ ማርክ ሩት ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።”አሁንም እየተነጋገርን ነው” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ኦፕሬሽኑ መቀጠሉንና ከኔቶ ኃላፊ ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን እንዲሁም ከካቢኔያቸው ጋር ልዩ ስብሳባ እንደሚያካሂዱ ገልጸዋል።

ፕሬዚደንት ካሮል ናውሮኪ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሚሳተፉበት ብሔራዊ የጸጥታ ቢሮ ስብሰባ ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጡ አስተቃዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *