የሕዳሴ ግድብ «አፍሪቃ ዕድል ፈንታዋን መወሰን እንደምትችል ትልቅ ማረጋገጫም ነው» አሉ የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ
የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚንስትር ሚያ ሞቲሊ በበኩላቸው «የአድዋ ድል ተምሳሌት ዳግም ተገለጠ « ሲሉ ግድቡን አሞካሽተዋል።
በሕዳሴ ግድብ የምርቃት ስነስረዓት ላይ የታደሙት የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን «ሥራዎትን ይግፉበት » በማለት አሞግሰዋቸዋል። የሕዳሴ ግድብ «አፍሪቃ ዕድል ፈንታዋን መወሰን እንደምትችል ትልቅ ማረጋገጫም ነው» ብለዋል። ለኢትዮጵያ ሕዝብ አገኛችሁ ላሉት «ትልቅ ስኬት» እንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የሕዳሴ ግድብ «አፍሪቃ ዕድል ፈንታዋን መወሰን እንደምትችል ትልቅ ማረጋገጫም ነው» ብለዋል። ለኢትዮጵያ ሕዝብ አገኛችሁ ላሉት «ትልቅ ስኬት» እንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሥነ ስረዓቱ ላይ ታዳሚ ከነበሩ የአገር መሪዎች ውስጥ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት የግድቡ ግንባታ ከኢትዮጵያዉያን በተጨማሪ ለአገራቸው ገጸ በረከት ይዞ መምጣቱን ያመለከቱበትን ንግግር አሰምተዋልል።
ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ሀገራቸው ከሕዳሴ ግድብ የኃይል አቅርቦት ለማግኘት ስምምነት እንደምትፈጽም አሳውቀዋል።
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ ” ዛሬ ቀኑ ለመላው የቀጣናው ህዝብ ታሪካዊ ነው ” ያሉ ሲሆን ” በቀጣናው ያለው ውሃና ሃብት በድንበር የተገደበ ሳይሆን የጋራ መፃኢያችንን የሚወስን ነው ” ብለዋል።
ሶማሊያ የጋራ መረጋጋት እና ብልፅግና የሁሉም ሃገራት ስሜት እና ጥቅም መጠበቅ ላይ ይመሰረታል ብላ እንደምታምን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ በቀጣናው ስለ ልማት መወራት ያለበት ከፉክክር አንፃር ሳይሆን ከትብብር አንፃር መሆን አለበት ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ሶማሊያ ከጎረቤቶቿና ከአጋሮቿ ጋር ለመነጋገርና ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ዝግጁ መሆኗንም አንስተዋል።
በአፍሪቃ ካሬቢያን የትብብር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ የመጡት እና በጉባ የሕዳሴ ግድብ የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የታደሙት የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚንስትር ሚያ ሞቲሊ «የአድዋ ድል ተምሳሌት ዳግም ተገለጠ « ሲሉ ግድቡን አሞካሽተዋል።
የአፍሪቃ ኅብረት ዋና ጸሐፊ መሀሙድ አሊ ዩሱፍ ኢትዮጵያ ፤ ሱዳን እና ግብጽ ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል። የአፍሪቃ ኅብረትም አገራቱ በንግግር ዘላቂ መፍትሄ ለመሻት የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን » አሳውቀዋል።
ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም
