ባንኩ ዛሬ ጳጉሜ 05 ቀን 2017 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ዋዜማን ምክንያት በማድረግ በማዕከሉ ህክምና ላይ ለሚገኙ ህፃናት ለበዓሉ ማክበሪያ የ250 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ይህ ድጋፍ ህፃናት በአዲስ ዓመት በአዲስ ተስፋ እና መልካም ምኞት እንዲጀምሩ ከመመኘት የመነጨ መሆኑን በፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ “የአዲስ ዓመት አከባበር የበለጠ ትርጉም ያለው የሚሆነው ለሌሎች ስናካፍል እና ቀጣይ ተስፋ ስናስብ ነው ብለዋል።
የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ህሩይ ዓሊ በበኩላቸው ለማዕከሉ በተደረገው ሰናይ ምግባር አመሰግነዉ ንብ ለብዙ ጊዜ በመሰል ተግባራት በመሳተፍ ከማዕከሉ ጎን መሆኑ ለልብ ታማሚ ህፃናት ተስፋ እንዲሆን አድርጓል ብለዋል፡፡
ማዕከሉ ከግለሰቦች፤ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት በሚደረግለት የተለያዩ ድጋፎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ይህ ማዕከል በኢትዮጵያን ለሚገኙ በርካታ ህጻናት ህይወት አድን የቀዶ ጥገና እና የልብ ህክምና ስራዎችን ይሰጣል፡፡
ለዓለም አሰፋ
ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም
