ዓለም አቀፍ ውሀ ላይ እየተንቀሳቀሰ የነበረው አነስተኛ ጀልባ ወደ አሜሪካ አደንዛዥ ዕፅ ይዞ እየሄደ ነበር ብለዋል ፕሬዝደንቱ።
ትራምፕ “አመፀኛ ዕፅ አመላላሾች ላይ” በተደረገ ጥቃት ሶስት ግለሰቦች መገደላቸውን ቢገልፁም ጀልባው ዕፅ ይዞ እንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረቡም።
ጥቃቱ የተፈፀመው፤ የቬንዙዌላው ፕሬዝደንት ኒኮላስ ማዱሮ ሀገራቸው ከአሜሪካ “ወረራ” ራሷን እንደምትከላከል ከገለፁ በኋላ ነው።
ማዱሮ የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “የሞት እና የጦርነት ጌታ” ሲሉ ዘልፈዋል።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት አሜሪካ፤ ደቡብ ካሬቢያን ላይ ፀረ አደንዛዥ ዕፅ ያለችውን ኦፕሬሽን አካሂዳ 11 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እየሻከረ መጥቷል።
“ዛሬ ንጋት በኔ ትዕዛዝ መሠረት የአሜሪካ ጦር ኃይል አመፀኛ እና ነውጠኛ የዕፅ አዘዋዋሪዎች ላይ ሁለተኛ ጥቃት ፈፅሟል” ሲሉ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገፃችው ፅፈዋል።
“እኚህ አደገኛ እና ነውጠኛ የዕፅ አዘዋዋሪዎች የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ ይደቅናሉ።”
ትራምፕ ውቅያኖስ ላይ ያለ አነስተኛ ጀልባ በጥቃቱ ሲወድም የሚያሳይ የ30 ሰከንድ ቪድዮም አጋርተዋል።
ከኦቫል ኦፊስ መግለጫ የሰጡት ትራምፕ፤ ጀልባው የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ስለመሆኑ ተመዝግቦ የተቀመጠ ማስረጃ እንዳላቸው አስታውቀዋል።
መስከረም 6/2018 ዓ.ም
